21/07/2026
****ግብይት ሲፈፅሙ አገልግሎት ሲጠቀሙ ሕጋዊ ደረሰኝ በመጠየቅ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ****
ለአንድ አገርና ከተማ ዘላቂ ዕድገት እንዲሁም ለተሻለ የሕዝብ አገልግሎት አቅርቦት ገቢ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። እኛ የምንከፍለው ግብርና የታክስ ክፍያ ወደ ከተማችን ልማት ተመልሶ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለመንገድ፣ ለንጹህ ውኃ አቅርቦት እና ለመሳሰሉት ማህበራዊ አገልግሎቶች ይውላል።
ለከተማችን ዕድገትና ለተሻለ ነገ የበኩላችንን አወንታዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ እነዚህን ተግባራት ያከናውኑ:
1. የVAT ደረሰኝ መቀበልዎን ያረጋግጡ፡ ማናቸውንም ግዢዎች ሲፈጽሙ ሕጋዊ የቫት (VAT) ደረሰኝ መጠየቅ።
2. የ5% አገልግሎት ክፍያ ደረሰኝ ይጠይቁ፡ የሆቴል ወይም የአልጋ አገልግሎት ሲጠቀሙ አዲሱን 5% የከተማ አገልግሎት ክፍያ የሚያሳይ ሕጋዊ ደረሰኝ መቆረጡን ያረጋግጡ።
- ያስታውሱ፡ ደረሰኝ መጠየቅ የከፈልነው ገንዘብ በቀጥታ ለከተማችን ልማት ገቢ መሆኑን ማረጋገጫ መንገድ ነው!
- ለአንድ ሀገርና ከተማ ገቢ ውሳኝ ነው VAT ደረሰኝ ና አዲሱን የከተማ አግልግሎት የገቢ ኮድ አልጋ ስትይዙ አግልግሎት ክፍያ 5% ደረሰኝ መቆረጡ ያረጋግጡ ለከተማ ገቢ የበኩልዎን አሰተዋጽኦ ያደረጉት
- ሕጋዊ ደረሰኝ በመጠየቅና በመቀበል ለከተማችንና ለሀገራችን ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣ!
13/01/2026