15/07/2025
ግብርን በወቅቱ በታማኝነት የመክፈል ጥቅሞች
ቀድሞ ግብር መክፈል ለግለሰቦችም ሆነ ለንግድ ድርጅቶች በርካታ ጥቅሞች አሉት።ከዚህ በታች ዋና ዋናዎቹ ቀርበዋል፦
ከቅጣት መዳን ፦ ግብር በወቅቱ አለመክፈል ወይም ዘግይቶ መክፈል የቅጣት ክፍያዎችን ያስከትላል። ቀድሞ በመክፈል እነዚህን ተጨማሪ ወጪዎች ማስወገድ ይቻላል።
የአዕምሮ ሰላም ፦ የግብር ክፍያ ሀላፊነት በጊዜው ማጠናቀቅ የአእምሮ ሰላም ይሰጣል። ግብር ከፋዩ ስለ ቀነ ገደብ ወይም ስለሚያስከትላቸው መዘዞች መጨነቅ አይኖርበትም።
የገንዘብ እቅድ ማውጣት ፦ ግብርን ቀድሞ መክፈል ግለሰቦች እና ድርጅቶች ገንዘባቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያቅዱ ያስችላቸዋል። የግብር ክፍያ በጀት ውስጥ በመካተቱ ድንገተኛ የገንዘብ እጥረት ወይም ጫና አይፈጠርም።
ከጭንቀት ነጻ መሆን ፦ የግብር የመጨረሻ ቀን ሲቃረብ የሚፈጠረውን ጭንቀት እና ግርግር ማስወገድ ይቻላል። ቀድሞ በመክፈል ሂደቱን በተረጋጋ ሁኔታ ማጠናቀቅ ይቻላል።
ጥሩ ስም መገንባት ፦ በተለይ ለንግድ ድርጅቶች፣ ግብራቸውን በወቅቱ ወይም ቀድመው መክፈል ለፋይናንስ ተቋማት እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ጥሩ የፋይናንስ ዲሲፕሊን እንዳላቸው ያሳያል። ይህ ደግሞ ብድር ለማግኘት ወይም ኢንቨስትመንት ለመሳብ ይረዳል።
የወለድ ክፍያ ማስወገድ ፦ ዘግይቶ በሚከፈል ግብር ላይ የወለድ ክፍያ ይጨምራል። ቀድሞ በመክፈል እነዚህን ተጨማሪ ወጪዎች ማስወገድ ይቻላል።
ያልተጠበቁ ሁኔታዎችን መቋቋም ፦ አንዳንድ ጊዜ የግብር አከፋፈል ሂደት ውስብስብ ሊሆን ይችላል ወይም ያልተጠበቁ ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ቀድሞ መክፈል ለእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ዝግጁ ለመሆን እና ለማስተካከል በቂ ጊዜ ይሰጣል።
11/07/2025
የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የግብር ከፋዩን ጥያቄዎች የሚመልስ ነው :- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
*******
የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ከዚህ በፊት ከግብር ከፋዩ የሚነሱ ጥያቄዎችን የሚመልስ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ ላይ የአስረጂ መድረክ አካሂዷል።
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ነፃ የተደረገው እስከ ብር መጠን 2000 የሚያገኙት ላይ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።
የ35 በመቶ የግብር ክፍያ መጠን መነሻው ከ14 ሺህ ብር በላይ በሆነ ደሞዝ ላይ መሆኑም በረቂቅ አዋጁ መካተቱ ተመላክቷል።
በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የገቢ ግብር አዋጁ ሳይሻሻል የቆየ በመሆኑ እና አሁን የተቀመጠው ምጣኔም መንግሥት ያገኝ የነበረውን ገቢ በመተው የተቀመጠ መሆኑን አስረድተዋል።
በግብር ሥርዓት ውስጥ ከተመዘገቡት ግብር ከፋዮች መካከል በትክክል ግብር የሚከፍሉት ከ63 በመቶ የማይሻገሩት መሆናቸውን አንስተው፣ የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ይህንን ክፍተት በመሙላት ፍትሐዊ የግብር ሥርዓትን የሚያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ የሕዝብ አስተያየት እንደሚሰበሰብበት በአስረጂ መድረኩ ላይ ተጠቁሟል።
በሳምሶን ገድሉ
#የገቢግብር
11/07/2025
በእሳት አደጋ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት መውደሙ ተጠቆመ
ደብረ ብርሃን፤ሀምሌ 3/2017 (ደብመኮ)፡-በደብረ ብርሃን ከተማ በእርጎ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት መውደሙ ተገለጸ፡፤
የእርጎ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ሥራ አስኪጅ አቶ በሃይሉ ተስፋዬ እንደገለጹት በአክሲዮን ማኅበሩ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት መውደሙን አስታውቀዋል፡፡
የእሳት አደጋው ሀምሌ 2 ከምሽ 3 ሰዓት አካባቢ ባላታወቀ ምክንያት መነሳቱን የጥበቃ ሠራተኞች ሪፖርት ማድረጋቸውን የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ በአደጋው የሞባይል፣የፍራሽ፣የጽህፈት መሳሪያ ሱቆች፣የህክምና አገልግሎት መስጫ ቢሮን ጨምሮ በሌላ አንድ ሱቅና በህንፃው ላይ ጉዳት ማድረሱን ዘርዝረዋል፡፡
በደብረ ብርሃን ከተማ የዐፄዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን ህሊና ግርማ በበኩላቸው የእሳት አደጋው መንስዔና ያደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ምርመራ እየተደረገ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡
የምርመራ ሥራው እንደተጠናቀቀም ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡ዘገባው የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ነው።
10/07/2025
ግብር ልማትንና ሰላምን ፋይናንስ ከማድረግ ባለፈ የመንግስት ጥንካሬ መለኪያ ነው።
08/07/2025
"የተቋማት አመራሮች የተሰበሰበውን ከመቀራመት ባሻገር ለዛ ምንጭ የሆነውን የመንግስትን ገቢ እንዲሰበሰብ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡" ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2017 የግብር ዘመን ግብር መሰብሰብ ስራ መጀመሩን የሚያበስር የንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር አካሄዷል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት ግብር ልማትን እና ሠላምን ፋይናንስ ከማድረግ ባለፈ የመንግስት ጥንካሬ መለኪያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡
የመንግስት ትልቅነትና ውጤታማነት ከሚለካባቸው ተግባራት ውስጥ ሠላምን መስከበር እና ግብር ማስከፈልና ማስተዳደር መቻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ተቋማት የተሰበሰበውን ከመቀራመት ባሻገር ለዛ ምንጭ የሆነውን የመንግስትን ገቢ እንዲሰበሰብ በማድረግ በኩል ያለውን መሰረታዊ ጉድለት መስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡
ከ2018 -2022 ዓ.ም በአማራ ክልል የሚተገበረው የአሻጋሪ እቅድ ያለ ጠንካራ መዋዕለ-ንዋይ ተግባራዊ ስለማይሆን ግብርን በወቅቱ መሰብሰብ፣ ማስተዳደርና ጥቅም ላይ ማዋል የቀጣይ ዓመት የመንግስት ትልቁ ተግባር እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
ግብር ቁልፍ የፋይናስ ምንጭ ስለሆነ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚሰጥ ተግባር፣ የአንድ ጊዜ ትኩረት ብቻ የሚሰጠው ስራ እንዳልሆነ እና የአመራሩን ትኩረት የሚጠይቅ የሁል ጊዜ ስራ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ማህበረሰቡ መሰረተ ልማት እንዳልተሟላለት በተለያዩ መድረኮች ይናገር እንጂ ይህን ፋይናንስ ለማድረግ የሚያችለውን ግብር እንዲሰበሰብ በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው የሚባል ስላልሆነ የከፈለን ግብር ከፋይ በማወደስና በማክበር የሚያጭበረብርን ደግሞ ሌባ ብሎ በግልጽ መናገርና ማረም ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረት ማህሙድ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ 408 ሺህ 171 የደረጃ "ሀ"፣ "ለ" እና "ሐ" & 116 ሺህ የኪራይ ገቢ፣ 92 ሺህ የሊዝ ገቢ እና 3 ሚሊዮን 657 ሺህ 148 የእርሻ ስራ ገቢ በድምሩ 4 ሚሊዮን 841 ሺህ 319 ከሚሆኑ ግብር ከፋዮች ገቢ እየሰበሰበ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ ከግብር ከፋይ ቁጥርና ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ አኳያ ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸው በ2017 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት በድምሩ 71 ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የክልሉ መንግስትና የገቢ ተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት 58 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 81 በመቶ መሰብሰብ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡
አሰራርን ማዘመን፣ የታክስ ማስከፈያ ምጣኔዎችን ማሻሻል& ግብር ከፋዮችን በደረጃቸው ከፍሎ አገልግሎት መስጠት፣ ያልተዳሰሱ የገቢ መሰረቶችን ማስፋትና በተቋሙ የሚታዩ የስነምግበር ችግሮችን እያረሙ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቶ ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል።
"ግብሬን ደስ ብሎኝ እከፍላለሁ"
08/07/2025
በደብረ ብርሃን ከተማ በአፄ Hርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ገቢዎች |ጽ/ቤት ሐምሌ 1/2017 ዓም የደረጃ ሐ የግብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደመቀ ፕሮግራም ተጀመረ ።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ የደብረብሃን ሪጅዮ ፓሊታን ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባየሁ ሞገስ ፣የመምሪያው ምክትል ሀላፈ አቶ ወንደስን ተገኝ ፣የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንደስን እሸቴ የጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ፅጌ ታዬ እንዲሁም የመምሪያ ደጋፊ የስራ ሂደት አስተባባሪ ዎች፣ባለሙያዎች እና ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ተገኝተዋል ።
የደብረ ብርሃን ከተማ ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባየሁ ሞገስ በመክፈቻ ኘሮግራሙ በከተማው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማጠናቀቅ ምንጩ ገቢ እንደመሆኑ ግብርን በታማኝነት እና በወቅቱ መክፈል እንደ ሚገባ ገልፀዋል።
የዘንድሮ ግብር የሚሰበስበው በኢታስ/ Etas/ ኤሌክትሮኒክስ በመሆኑ ግብር ከፋዩ በስልኩ መልእክት የታክስ ዉሳኔ የሚላክለት ሲሆን መልእክቱ ሲደርሰው በቴሌ ብር ወይም ከሰባቱ የባንክ አማራጮች በሚመቻቸው ግብራቸውን እንዲከፍሉ በማስገንዘብ በሂደት ለግብር ከፋዩ እያስተዋወቅን የተመዘገቡትን ወደግብር ስርአቱ በማሸጋገር ከከፈሉ በኋላም የንግድ ፈቃዳቸውን ክሊራንስ መውሰድ ሳያስፈልጋቸው ወዲያውኑ ማደስ እንደሚችሉ ማስገንዘብ ይጠበቅብናል በማለት መልእክታቸውን አሰተላልፈዋል።
አያይዘውም ይህንን ተግባር የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተግባሩን በጥብቅ ዲሲፕሊን ይዘው ወደስራ መግባት እና ቅድመው የሚመጡ ግብር ከፋዮችን ማስተናገድ አለብን ብለዋል።
በመጨረሻም ክፍለ ከተማው ለተከታታይ ሁለት አመታት በገቢ የተሻለ አፈፃፀም ያለው ክፍለ ከተማ በመሆኑ ለዚህ ውጤት የላቀ ተሳትፎ ለነበራቸው አመራሮች ባለሙያ ዎችና ለግብር ከፋዮች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበ ዋል ።
የአፄዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንደሰን እሸቴ በበኩላቸው ይህንን አዲስ የግብር ማስከፈያ ሲስተም በፈጠነ መንገድ ተረድተን የንግዱ ማህበረሰብ ሳይንገላታ ጊዜውን ሳያባክን እንዲስተናገድ ጊዜያችንን መስዋዕት አድርገን ከሌሎች ክፍለ ከተሞች በተሻለ ውጤት መፈፀም አለብን በማለት መልእታቸውን አስተላልፈዋል።
07/07/2025
የደረጃ ሐ ግብር ለመሰብሰብ የሚያስችል የክረምት የን ቅናቄ እቅድ ላይ ከጠቅላላ ሠራተኞች ጋር ው ይይት ተደረገ ==
ሰኔ 30/2017 .ዓም
****************
የደብረብርሃን ከተማ የአፄ ዘር ዓ ያዕቆብ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኞች ግብሬን ደስ ብሎኝ እከፍላለሁ! በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 1 / 2017 ዓ.ም የሚጀመረውን የደረጃ ሐ ግብር አሰባሰብ የንናቄ ዕቅድ ላይ ውይይት አደረጉ ::
በንቅናቄ መርሃ ግብሩ ላይ የንቅናቄ አቅዱ አላማ ግብ እንዲሁም መርሀ ግብሩ መቼ እንደሚከናወን በዝርዝር ቀርቧል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የጽ/ቤትሀላፊ ወ/ሮ ፅጌ ታዬ ተገኝተዋል ::
በንግግራቸውም በተያዘው በጀት ዓመት በገቢ እቅድ አፈጻፀም የተሻለ ገቢ መሰብሰብ መቻላቸውን እና የተገኘው ውጤትም የአመራሩ እና የባለሙያው በመሆኑ ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት በሙሉ በተቋሙ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ።
የ2017 የደረጃ ሐ የግብር ንቅናቄ ከሌላው ዓመት ለየት ያለ እና የ ኢታስን ኣገልግሎት ተጠቅመን አገልግሎት አሰጣጣችንን በማሻሻል ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ግብር ከፍዮቻችንን የምናስተናግድበት ወቅት ነው ።
በመሆኑም ከሌሎች ክፍለ ከተሞች ተወዳዳሪ በመሆን ተግባሩን ለመፈፀም ቁርጠኛ ሆነን የእረፍት ጊዜያችንን ጭምር በመጠቀም መረጃችንም ቅሬታ በማያስነሳ መልኩ በሲስተም በማደረጃት እና ለግብር ከፋዩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ግብራችንን በአጭር ጊዜ መሰብሰብ አለብን የደረጃ ለ ግብርም አሳውቀው ግብራቸውን የሚከፍሉት ጻጉሜ5/6 2017 ዓ.ም በመሆኑ መቀስቀስ አለብን ብለዋል።
ከተሳታፊዎችም በኢታስ ስንስራ መብራት ቢጠፋ ምን ምቹ ሁኔታ አለ? የንቅናቄ ዕቅዱ ለምን ዘገየ? በውቅቱ ቢቀርብ ? ቴክኖሎጂው አዲስ ከመሆኑጋር ተያይዞ የተሰጠው ስልጠና በቂ አይደለም ? ለውጤቱ መሳካት ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ብንሰራ ? ተግባሮችን ስንስጥ ለመጠያየቅ እንዲያመች ባለቤት ቢኖራችው ? ለግብር ከፋዩ ግንዛቤ ቢፈmርለት ? የሚሉትጥያቄዎች ተነስተዋል።
በመጨረሻም ለተነሱት ጥያቄዎች የጽ/ቤተ ሀላፊ ማጠቃለያ ሐሳብ ሰጥተው ሐምሌ 1/2017ዓ.ም የሚጀመረውን የደረጃ ሐ ግብር አሰባሰብ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ጥሪ የተደረገላቸው አመራሮች ባለሙያዎች እና ግብር ከፋዮች እንዲገኙ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
04/07/2025
የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የቁርጥ ግብራቸውን በቴሌብር አማካኝነት ለመሰብሰብ የሚያስችል አሰራር ላይ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
(አፄ ዘርአ ያዕቆብ ፣ሰኔ 26/2017ዓ.ም)
የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የቁርጥ ግብራቸውን በቴሌብር አማካኝነት ለመሰብሰብ የሚያስችል አሰራር ላይ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።
በቴክኖሎጂ የታገዘ የታክስ ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በኢ-ታክስ አተገባበር ላይ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ ስልጠና በአፄዘርአያዕቆብ ክፍለከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።
ስልጠናውን በጀት ዓመት የግብር መክፊያ ወቅት መድረሱን ተከትሎ የጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የታክስ ዉሳኔያቸዉን በእጅ ስልካቸዉ ማሳወቅ እና ግብር ከፋዮችም ባሉበት ሆነዉ ግብራቸዉን በተለያዩ የክፍያ አማራጮች እንዲከፍሉ የሚያስችል አተገባበር መሆኑን በስልጠናዉ ተብራርቷል።
የስልጠናው ዓላማ በዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎችን በአሰራሩ ላይ ስልጠናን በመውሰድ የኢ-ታክስ /የኤልክትሮኒክስ ታክስ ስርዓት/ አገልግሎት በቴሌ ብር አማካኝነት በመዘርጋት ግብር ከፋዩን በመመላለስ የሚያጠፋውን ግዜና እንግልት የሚያስቀር ፍትሃዊና ቀልጣፋ የሆነ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለመዘረጋት መሆኑን አስተባባሪው አያይዘው ገልፀዋል።
የዘገበው የአፄ ዘርአ ያእቆብ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ግብር ትምህርት እና ኮሚዮኒኬሽን ነው ።
03/07/2025
ግብርን በተመለከተ....
የታክስ ስርዓት አስተዳደር ችግር ያለበት ነው የግብር ስወራ ችግርም አለ ነገር ግን ግብርን ዲጅታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው እሱም ውጤት እያመጣ ነው በታማኝነት ግብርን መከፍል ካልተተቻለ መንገድ የለም ጤና የለም ሰላም የለም የምንፈልገውን መሰረተ ልማትም ማሟላት አንችንችልም ስለዚህ በንግድ ላይ የተሰማሩ አካላት በሙሉ በታማኝነት ግብር መክፈል አለባቸው።
26/06/2025
የደርጃ "ሐ"ግብር ከፋዮች ሀምሌ 1/2017 ጀምሮ ለሚከፈለው ግብር በሲስተም ለመወሰን እና ለማስተዳደር በወጣዉ አሰራር ስርዓት ላይ በzoom meeting ስልጠና በመሰጠት ላይ ።
11/06/2025
መንግስት የነዳጅ ሽያጭ ላይ 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ሊጀምር ነው
| ከመጭው ሐምሌ ወር ጀምሮ የነዳጅ ግብይትን በአለም አቀፉ ዋጋ መሰረት ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ላለፉት ወራት ቀስ በቀስ የነዳጅ ድጎማን እያነሳ ያለው መንግስት ሙሉ በሙሉ ድጎማውን ከማቆም ባሻገር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስከፍልበት ማቀዱ ተሰምቷል፡፡
የፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት እንደሚያሳየው ከነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 15 በመቶ ቫት በማስከፈል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን ያሳያል፡፡
የፌዴራል መንግስት የ2018 የገቢ በጀት በሚል ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ በጀት ከስኳርም 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እና ከጨው 337 ሚሊየን ብር ተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብ መታቀዱን ያሳያል፡፡
ከዚህ ቀደም እንደ ዘይት እና ስኳር ያሉ ምርቶች በመንግስት የሚደጎሙና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ እንዲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የነበሩ መሆናቸው አይዘነጋም፡፡
#ሸገር ሬድዮ