Sele Tax - ስለ ታክስ

Sele Tax - ስለ ታክስ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sele Tax - ስለ ታክስ, አዲስ አበባ, Addis Ababa.

14/08/2025

ለግንዛቤዎት! በሒሳብ ምርመራ ወቅት ለውሳኔ አሰጣጥ አሻሚ የሚሆኑ የተለዩ ዝርዝር ጉዳዮች
=========
#የወለድ ወጪ ሊፈቀድ የሚችለው ግብር ከፋዩ ለንግዱ የወሰደውን ብድር ለንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ማዋሉን ሲያረጋግጥ ነው በማለት የሚደነግግ በመሆኑ ይህን ድንጋጌ ከግምት በማስገባት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
# የግብር ከፋይን የማርጅን (የትርፍ ህዳግ) ማስተካከያ በማድረግ የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#በአጠራጣሪ እና በሀሰተኛ ደረሰኝ ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
# ግብር ከፋዩ ከፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ከግለሰቦች ለረጅም እና ለአጭር ጊዜ የሚወስዱትን ብድር ባለመመዝገብ ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ከካፒታል ማሳደግ ጋር በተያያዘ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ፣
#በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማራ ግብር ከፋይ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ያገኘውን ገቢ እና ለፕሮጅክቶቹ ያወጣውን ወጪዎች በአመዘጋገብ ክፍተት ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#በተሰብሳቢ እና በተከፋይ ሒሳቦች አያያዝ እና ምዝገባ ክፍተቶች ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ጉልህ ግዢዎችን ሊረጋገጥ በሚችል በባንክ የክፍያ ስርዓት ባለማከናወን ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#በምርት ሂደት አምራቾች የሚያመርቱት እቃ ግብዓት ምርት ጥመርታ ባለመለየታቸው የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ግብር ከፋዩ ግዢውን፣ ሽያጩን እና በእጅ ላይ ያለውን እቃ በተመሳሳይ ስያሜ እና መለኪያ ባለማስቀመጥ ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ግብር ከፋዩ የባንክ ሒሳብ እንቅስቃሴ የሒሳብ አያያዝ ክፍተት ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ህንጻው የተገኘበት ወይም የተገዛበት ወይም የተገነባበት ዋጋ ላይ በሚገኝ ልዩነት መሰረት በማድረግ የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
ማስረጃ የማይገኝላቸውን ግዢዎች በተመለከተ ሊረጋገጥ በሚችል የክፍያ ስርዓት ክፍያዎችን ባለመፈጸም የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ከተከፋይ ሒሳብ ላይ ተቀናሽ የሚደረጉ ዊዝሆልዲንግ ደረሰኞች (withholding invoice) በተገቢው ባለመያዝ የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#በ3ኛ ወገን በሚገኙ መረጃ መሰረት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#በሂሳብ ምዝገባ ወቅት የጥሬ ገንዘብ አሉታ (ካሽ ኔጌቲቭ) በመሆኑ ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፤
#ግብር ከፋዩ በተለያዩ ጊዜ ከንግዱ ውጪ በሚያደርገው የጥሬ ገንዘብ ዝውውር በአግባቡ ባለመመዝገብ ምክንያት የሚወሰኑ ውሳኔዎች፣

03/08/2025

ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ የሚያስተላልፉ ወኪሎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀማጭነታቸውን አሜሪካ ያደረጉና በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፉ የሃዋላ ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ፈቃድ ያላቸውና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች መጠቀም ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ለአሸባሪዎች የሚደረግ ድጋፍን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።

በአንጻሩ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝነት ለመቀነስና የገበያ ምንዛሪ ዋጋን ለማዛባት በማለም በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩ መኪሎች መኖራቸውን አመልክቷል፡፡

በተጨማሪም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ አባላት የተሰበሰበን ገንዘብ ሕገ ወጥ ተግባርን ለመደገፍ የሚውሉና ገንዘብ በማሸሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ አስተላላፊዎች መለየታቸውን ነው ያስገነዘበው፡፡

በዚህ መሰረትም፡-

1. ሽገይ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪል ( Shgey Money Transfer)

2. አዱሊስ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪል (Adulis Money Transfer) USA)

3. ራማዳ ፔይ (Ramada Pay (Kaah)

4. ቲኤኤጄ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪል (TAAJ Money Transfer)

የተሰኙ የሃዋላ ተቋማት ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ እንደሚያስተላልፉ ተጠቁሟል፡፡

የወኪሎችን እንቅስቃሴ ለመመርመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን የጠቀሰው ባንኩ ÷ ምርመራውን አጠናክሮ በመቀጠል ተገቢ ርምጃ እንደሚወስድ አስገንዝቧል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ፈቃድ በሌላቸው የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪሎች ገንዘባቸውን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ከመላክ እንዲቆጠቡም አሳስቧል፡፡

በእነዚህ ወኪሎች በኩል የተላከ ገንዘብ ሊወረስ እንደሚችል እና ከተላከ በኋላ ለተፈለገው አካል ስለመድረሱ ምንም አይነት ዋስትና እንደሌለም አመልክቷል።

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ እና አስተማማኝ መንገዶችን በመጠቀም ገንዘባቸውን እንዲጠብቁም አስገንዝቧል፡፡

ሕጋዊ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪሎችን ሙሉ ዝርዝር ከታች በተቀመጠው የብሔራዊ ባንክ ድረ ገጽ ላይ ማግኘት እንደሚቻልም ባንኩ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡

403 Forbidden

21/07/2025
17/07/2025

ታክስ ከፋይ ማሳወቅ ያለበት ለውጥ
===========================
ማንኛውም ለታክስ ከፋይነት የተመዘገበ ሰው ስም ወይንም የሚከተሉት ዝርዝር ጉዳዮች ለውጥ ሲደረግባቸው ታክስ ከፋዩ በ30 ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ በጽሑፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

ለውጦቹም፡-

▶ በንግድ ድርጅቱ ስያሜ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በድርጅቱ ስም የተመዘገበ:-
i. ቋሚ የንግድ ሥራ፣ የቢሮ እና የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ፤
ii. በማምረቻ ቦታ ወይም ታክስ ከፋዩ በሚጠቀምበት መጋዘን ላይ የተደረገ
የአድራሻ ለውጥ፤
iii. በፖስታ ወይም በመደበኛ እና በተንቀሳቃሽ ሰልክ፣ ፋክስ ወይም ኢ-ሜል
አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በዋነኛ የሥራ እንቅስቃሴው ወይም በቅርንጫፍ ወይም በንግድ ሥራው ዘርፍ
ወይም መስክ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ወይም የመመስረቻ ጽሑፍ ወይም የሽርክና
ስምምነት ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በአክሲዮን ባለድርሻ አባላት ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በድርጅቱ ወይም በታክስ እንደራሴው የባንክ ሂሳብ ወይም የባንክ ቅርንጫፍ
አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በታክስ እንደራሴው እና ከሚኒስቴሩ ጋር ግንኙነት በሚያደርግበት
የኤሌክትሮኒክስ አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ በተመዘገበና በተከፈለ ካፒታል ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ የንግድ ሥራውን በከፊል ወይም በሙሉ በማቋረጥ ወይም በሽያጭ ወይም
በስጦታ በማስተላለፍ ወይም በመለወጥ ወይም በዋስትና በማስያዝ በድርጅቱ ላይ
የተደረጉ ለውጦች፤
▶ በንግድ ሥራ ወኪል ወይም የታክስ እንደራሴ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
▶ የአክሲዮን ትርፍ ድርሻ ለካፒታል ማሳደጊያ ሲውል፤
▶ የገቢ ምንጭ መቋረጡን ወይም መሻሻልን በተመለከተ፤
• የቤት ወይም የህንፃ ወይም የመጋዘን ኪራይ ውል ሲቋረጥ ወይም
ሲሻሻል፤
• በተሽከርካሪ ወይም በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ወይም ሌሎች የካፒታል
ወይም የንግድ ሥራ እቃዎች ላይ የተደረገ የኪራይ ውል መቋረጥ ወይም
መሻሻል፤
• በራሱ ገቢ የሚያስታውቅ ተቀጣሪ ሥራውን ሲለቅ ወይም ሲቀይር ወይም
የደመወዝ ለውጥ ሲኖር፤
• የንግድ ሥራ እንቅስቃሴውን በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ሲያቋርጥ ወይም
ሲያሻሽል እንዲሁም
▶ የታክስ ከፋዩ ሠራተኛ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ወይም የሠራተኞች
የደመወዝ ለውጥ ሲያደርግ፤

ምንጭ:- ገቢዎች ሚኒስቴር

06/07/2025

የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ሊሻሻል መሆኑ ተገለፀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። ረቂቅ አዋጁ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍም ተወስኗል።
ይህ ማሻሻያ አሁን ካለዉ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ፣ በነበረው አዋጅ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች ለመድፈን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ የግብር ስርዓቱ መሰረታዊ የግብር መርሆችን (ታክስ ፕሪንሲፕልስ) የሚያሳካ በሚያስችል መልኩ እንዲቀረጽ መደረጉ ታውቋል።

05/07/2025

ማህበረሰቡ ዕለት በዕለት የሚሸምታቸው ያልተዘጋጁ የአትክልት ምርቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መደረጋቸው ተገለፀ፡፡

ሰኔ 28 ቀን 2017ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በላከው ሰርኩላር ያልተዘጋጁ እንደ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች የአትክልት ምርቶች ከቫት ውጭ መደረጋቸው አሳውቋል፡፡
ቢሮው በዛሬው ዕለት ባወረደው በዚሁ ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 አንቀፅ 10 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 570/2017ዓ.ም መሰረት ያልተዘጋጁ እንደ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች ያሉ ምርቶች ወደሀገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ ተመርተው ለግብይት ሲቀርቡ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መደረጋቸውን ተደንግጓል ሲል አስቀምጧል፡፡
በዚህም መሰረት ከላይ የተገለፁ ያልተዘጋጁ የአትክልት ምርቶች የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች ብቻ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ መሆናቸው ታውቆ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ተገቢው ክትትል በማድረግ እንዲፈፀም አሳውቋል፡፡
ይሁንና በአዋጁ ከታክስ ነፃ ከተደረጉ ውጪ የፍራፍሬ ምርቶች የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች የቫት አሰራሩ የሚቀጥል መሆኑንም በመግለፅ ተገቢው ክትትል እንዲደረግ አሳስቧል፡፡

01/07/2025

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጽድቋል።

በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ " መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም " ብሏል።

የኢትዮጵያዊያንን መብት በማይነካ መልኩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ሥራዎች ይሰራሉ ሲል ገልጷል።

የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው።

የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ሲሆን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ ይሄዳል ተብሏል።

01/07/2025

የንብረት ታክስ በክልሎች በሚቀጥለው በጀት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክልሎች የንብረት ታክስን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራሉ " አሉ።

ይህን ያሉት በህዝብ ተ/ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

" ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እዳ እየከፈለ የሚገኘው መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ገቢ እያገኘ መምጣቱን መጥቷል " ያሉ ሲሆን " ገቢ የማያስገኝ አገልግሎት አክሳሪ ነው " ብለዋል።

በአዲስ አበባ የንብረት ታክስ ክፍያ ተግባራዊ መደረጉን በማስታወስ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት የንብረት ታክስ በክልሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀመራል " ነው ያሉት።

13/06/2025

በግብይት ወቅት ከ 10,000 ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም፤ ለከፋዩ በወጪነት፣ ለተቀባዩ ደግሞ አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጣልበት ያደርጋል ተባለ።

አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ሲጸድቅ ከ10,000 ብር በላይ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መፈጸም የሚያስቀጣ ይሆናል ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁ ላይ ሃሳብ ለማዋጣት ከተሳተፉ ባለሙያዎች የተወሰኑት ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው አሰራር ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው አቶ ተወዳጅ መሐመድ እንዳሉት አዋጁ ተግባራዊ የሚደረገው በጥሬ ገንዘብ የሚፈፀም ግብይትን መገደብን ታሳቢ አድርጎ ነው።

በአንድ ግብይት የሚፈፀም የጥሬ ገንዘብ ክፍያ ከ10ሺህ ብር ከበለጠ፣ ትርፉ ብር ለከፋዩ በወጪነት አይያዝም።

ገንዘቡን የተቀበለውም የትርፉን ገንዘብ እጥፍ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣልበት ተቀምጧል።

ለምሳሌ ፦ የ20,000 ብር ግብይት በጥሬ ገንዘብ ቢፈፀም ለነጋዴው፣ ከ10 ሺህ ብር በላይ ያለው በወጪነት አይያዝም፣ ለተቀባዩ ደግሞ ከ10,000 በላይ ያለው ቀሪ 10,000 ብር እጥፍ ማለትም 20,000 ብር ይቀጣል እንደማለት ነው።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተሳተፉ፣ በጥሬ ገንዘብ ግብይት እንዲፈፀም ምክንያት የሚሆነውን በንግድ ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ችግር መፍታት የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችልና፣በሌሎች መመሪያዎች የጥሬ ገንዘብ ግብይት ስለሚፈቀድ አዋጁ የተናበበ እንዲሆን ጠይቀዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ባሰናዳው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ከ10,000 ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ግብይት እንዳይፈፀም የሚጣለው ግዴታ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ በባንኮችና በማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም ይላል።

ሌሎች አዋጁ ተፈፃሚ የማይሆንባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ዝርዝራቸው ይፋ ይሆናል ይላል ረቂቁ።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

11/06/2025

#ለመረጃ፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ የመጀመሪያ ረቂቅ አዘጋጅቷል! የረቂቁን የአማርኛ ቅጂ ማንበብ ለምትፈልጉ

Telegram: Contact @seletax

06/06/2025

የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ሬድዮ ጣቢያው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።

በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተለይ ቋሚ ደመወዝተኛው የኑሮ ጫናውን ለመቋቋም እንዲችል የሚቆረጥበት የገቢ ግብር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሻሻልለት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ?

የኢትዮጵያ ብር እና የኬንያ ሽልንግ ከዶላር አንፃር የምንዛሪ ዋጋቸው እኩል ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከ600 ብር ጀምሮ የሚያገኝ ደመወዝተኛ የገቢ ግብር ይቆረጥበታል፤ በኬንያ ደግሞ የገቢ ግብር የሚቆረጠው ከ24,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ደመወዙ 10,900 ብርና ከዚያ በላይ የሆነ ተቀጣሪ 35 በመቶ የገቢ ግብር ሲቆረጥበት፤ በኬንያ ከ800,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው 35 በመቶ የገቢ ግብር የሚቆረጥበት፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

28/05/2025

በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን በአገር ውስጥ ማምረትም ሆነ መገጣጠም ተከለከለ
በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ወደ 500 ሺሕ የማድረስ ዕቅድ መያዙ ተገልጿል
• በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች በአገር ውስጥ እንዳይመረቱና እንዳይገጣጠሙ መታገዱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ
• የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የቻይናው ሁዋጂያን ኩባንያ ከጂኤሲ አዮን ኩባንያ ጋር በመተባበር ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ባስተዋወቀበት መድረክ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ታበረታታለች ብለዋል፡፡
• ‹‹በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እናበረታታለን፡፡ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይመረቱ፣ እንዳይገጣጠሙና ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን፡፡ የምናበረታታው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ እንዲመረቱ፣ እንዲገጣጠሙና ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ነው፤›› ብለዋል፡፡

• ‹‹ሙሉ ለሙሉ በአገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ታክስ አይከፍሉም፡፡ በፈጣን ቻርጂንግ የሚሰማሩ ከሆነም ሙሉ ለሙሉ ከታክስ ነፃ ናቸው፡፡ በታዳሽ ኃይል የሚሠሩ ሆነው ሙሉ ለሙሉ በውጭ አገር የተገጣጠሙ ከሆኑ ደግሞ 15 በመቶ ብቻ የጉምሩክ ቀረጥ ይከፍላሉ፤›› በማለት ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡
• ‹‹በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር 500 ሺሕ የማድረስ ዕቅድ አለን፡፡ አሁን ቁጥራቸው ከ110 ሺሕ በላይ ደርሷል፡፡ ከባለሁለት ጎማ ጀምሮ እስከ የከተማ አውቶቡሶች በአገር ውስጥ እየተገጣጠሙ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Accountant in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Culinary Team

Attire

Website

Address

አዲስ አበባ
Addis Ababa