AZE Authorized Accounting and Consulting Firm

AZE Authorized Accounting and Consulting Firm

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from AZE Authorized Accounting and Consulting Firm, NK Building behind Dembel and Bole Infront of Ethio Ceramics Around Japan Embassy Genete Limat Building
Office No. 755/19, Addis Ababa.

07/06/2025

My client needs to hire in a senior accountant position if any one interested and fit for a position you can send me your documents via email [email protected]

19/04/2025

ETICPA, ሚናውን ሊወጣ በደጅ ቆሟል፡፡
ኢትዮጵያ ከ120 ሚሊዮን በላይ ለሆነ ህዝብ ከ600 የማይበልጡ ፕሮፌሽናል አካውንታንቶች፣ ከዚህ ውስጥ ከ150 የማይበልጡ የውጪ ኦዲተሮች እና ሁለት ሺህ የማይሞሉ በሙያው ዓለም አንቱ የተባሉ፣ ልምድ እና አቅም ያዳበሩ የተፈቀደላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ያሏት ሀገር ናት፡፡ ይህ ቁጥር በየትኛውም የምድራችን ሀገራት ከፍላጎት እና አቅርቦት አንፃር ለምጥጥን የማይቀርብ አሳሳቢ ቁጥር መሆኑ በሀገሪቱ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ እና ኦዲት ጥራት ላይም የጎላ ጉዳት ቢያስከትል ላይገርም ይችላል።

አዋጅ 847/2006 የመደንገጉ እና አዋጁን ለማስፈፀም የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ እንደ ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት እና የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ደግሞ በሙያዊ ሥነ-ምግባር የታነፁ ባለሙያዎችን በማፍራት እና በማብቃት ዓለም ዓቀፍ የሂሳብ እና ኦዲት ስታንዳርዶችን መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዘጋጀት በሀገሪቱ ጤናማ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ ትርጉም ያለው ሚና እንዲወጡ ትልቅ ተልዕኮ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሆኖም ጠንካራና የተደራጀ የፕሮፌሽናል አካውንታንት ኢንስቲትዩት ሳይኖር ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት ብቻውን መፈጠሩ ከፈረሱ ጋሪውን ሳያስቀድም እንዳልቀረ ያስጠረጥራል፡፡ ሆኖም ቀድሞ የተፈጠረው ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት ተልዕኮውን ለማሳካት የቦዘነበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ግን ማሳካት የሚችለው በህግ ሊወጣው የሚገባውን ብቻ ሲሆን ምንም ያክል አንዱ የአንደኛውን ሚና ሊተካ ባይችልም በተለይ ሙያውን በማስተዋወቅ፣ በማስተማር እና በማዘጋጀት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ለኢንስቲትዩቱ መቋቋምም የተጋውን ያክል ተሳክቶለት አሁን እውን ሆኗል፡፡

በአዋጁ የተጠቀሰው ኢንስቲትዩት ብቁ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎችን ማፍራት እና ሙያዊ ብቃታቸውን ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ፣ ቀጣይነት ባለው ስልጠና ሙያዊ አቅም ማጎልበት፣ አዳዲስ በሚወጡ እና የሚሻሻሉ የዘርፉ ስታንዳርዶችን እየተከታተለ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና ለስራ ብቁ ማድረግ ይጠበቁበታል፡፡ ያለ ጠንካራ ኢንስቲትዩት፣ የሂሳብ ባለሙያዎችን ለቀጣይ ሙያዊ እድገት ማጨት፣ ክህሎትን ለማሻሻል እና ጊዜውን የሚመጥን አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን የማግኘት እድሎች ያነሱ ናቸው።

ሙያው ውስብስብ እና ተለዋዋጭ የሂሳብ ደረጃዎችን፣ የቁጥጥር መስፈርቶችን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ወደ ላቀ ደረጃ እያደገ የሚገኝ ሲሆን ባለሙያው እግር በእግር በመከተል ተወዳዳሪነቱን ማረጋገጥ፣ ከተለምዷዊ አሰራር እየተላቀቀ እና ከዓለም እየተቀላቀለ አዳዲስ ክህሎቶችን እየቀመረ የሀገር ኩራትነቱን ማስመስከር ይጠበቅበታል፡፡ ይህ በግል ጥረት ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር በባለቤትነት ተቀብሎ የህግ አካል አድርጎ የሚያስፈጽም አካል ያስፈልጋል፡፡ የETICPA መቋቋም ዋና ዓላማም ለዚሁ ነው፡፡ ሙያው ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቁን እና የህዝብ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጡን ለመቆጣጠርም AABE የአንበሳውን ሚና በመወጣት ከኢንስቲትዩቱ ጎን ይቆማል፡፡

19/04/2025

"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግፃፅ በርሱ ላይ ነበረ፥ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።" ኢሳ 53፤5
እንኳን ለብርሀነ ትንሣኤው በሠላም አደረሰን!☦️
መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንልን✨️✟🕊

Want your business to be the top-listed Accountant in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Culinary Team

Attire

Telephone

Website

Address

NK Building Behind Dembel And Bole Infront Of Ethio Ceramics Around Japan Embassy Genete Limat Building Office No. 755/19
Addis Ababa