11/09/2024
To all Ethiopians Happy New Year 2017 E.c
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yitbarek Mekonnen Authorized Accountant, Accountant, kirkos subcity werda 03 Street Meskelflower, Addis Ababa.
This is our mission to simplify the accountancy service of any business sector and satisfies our customers needs by delivering our service like consultation, report preparation, system design, IFRS conversion and other financial service ...
11/09/2024
To all Ethiopians Happy New Year 2017 E.c
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንኮች ከቀውስ ይታደጋል፣ መረጋጋትም ያሰፍናል ያላቸውን አምስት አዳዲስ መመሪያዎች ይፋ አድርጓል። መመሪያዎቹ ከዚህ ቀደም የተወሰዱ ብድሮችንም ሆነ አዲስ የሚሰጡ ብድሮች ላይ ገደብ እና ተጨማሪ ተጠያቂነትን ይዟል። መመሪያው በሀገሪቱ ባሉ ባንኮች ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚከሰቱ አዳዲስ ለውጦችን ለመገንዘብ የመመሪያዎቹን አንኳር ይዘት እንደሚከተለው አሰናድተነዋል። አንብቡት
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ጤንነት ያስጠብቃል ያላቸውን አምስት መመሪያዎችን አሻሽዬ አውጥቻለሁ ባለው መግለጫ ላይ የንግድ ባንኮች ለደንበኞቻቸው ብድርን የሚያራዝሙበትን መንገድ የሚገድብ መመሪያን አሻሽሎ ማውጣቱን ገልጿል።
ማዕከላዊ ባንኩ የብድር ጊዜ ማራዘምን የሚገድበው የተሻሻለው “የንብረት ምደባ እና ለተዛማጅ ስጋቶች ስለሚያዝ የመጠባበቂያ ፕሮቪዥን” ፣ የሚለው መመሪያ ነው። በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም ንግድ ባንኮች የአጭር እና የመካከለኛ ጊዜ ብድሮችን የመክፈያ ጊዜ ማሻሻል የሚፈቀድላቸው ሶስት ጊዜ ብቻ እንዲሆን ገድቧል።
ከዚህ ቀደም ንግድ ባንኮች የአጭር እና መካከለኛ ጊዜ ብድሮችን አምስት ጊዜ ማራዘም ወይንም የብድር ውልን ማሻሻል ይፈቀድላቸው ነበር። ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ ብድርን የመክፈያ የውል ጊዜን ማሻሻል የሚፈቀድላቸው ለአራት ጊዜ ብቻ እንዲሆን በብሄራዊ ባንኩ በተሻሻለው መመሪያ ደንግጓል። ከዚህ ቀደም የረጅም ጊዜ ብድር መክፈያ ጊዜን ለስድስት ጊዜ ማራዘም ይፈቀድ ነበር።
ማዕከላዊ ባንኩ የብድር መክፈያ ጊዜ የማራዘምያ ድግግሞሽን መገደብ ያስፈለገው በንግድ ባንኮች ዘንድ ብድሮችን ሁል ጊዜ ጤናማ አድርጎ የማቅረብ ልማድን ለማስቀረት መሆኑን ገልጿል። በተለይ የብድር መክፈያ ጊዜን በተደጋጋሚ ማራዘምን በርካታ ባንኮች በየአመቱ ያልተገባ ትርፍን ለማግኘት እንደሚጠቀሙበት ብዙ ጊዜ ይነሳል።
አንድ ተበዳሪ ብድሩን በወቅቱ መክፈል ካልቻለ አበዳሪው ባንክ መመለስ ያልቻለውን ያክል ገንዘብ በመጠባበቂያነት መያዝ ይጠበቅበታል።ሆኖም የብድር መክፈያ ጊዜው የሚራዘም ከሆነ ግን ለመጠባበቂያነት የሚያዘው ገንዘብ ወደ ትርፍነት የመሄድ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው።
በተሳሳተ ሁኔታ ሁል ጊዜ ብድርን ጤናማ አስመስሎ ማቅረብ ለባንኮች ለጊዜው ትርፍ ማግኛ ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት ለፋይናንስ ዘርፉ አደጋን ማምጣቱ አይቀርም። ለዚህም ብሄራዊ ባንኩ የብድር ማራዘሚያ ድግግሞሽን እንዲገደብ አድርጓል። ማዕከላዊ ባንኩ አንድ ብድር የመክፈያ ጊዜው ሳይደርስ በተለያየ ሁኔታ ሳቢያ የመከፈል እድሉ የጠበበ መሆኑን አመላካች ነገር ካለ እንደ ተበላሸ ብድር ተቆጥሮ ቢያንስ አጠራጣሪ ብድሮች ውስጥ እንዲገባ ባሻሻለው መመሪያ ደንግጓል።
በሌላ በኩልም አንድ ተበዳሪ ከአንድ ባንክ የተለያዩ ብድሮች ወስዶ ከብድሮቹ አንዱ የተበላሸ ሆኖ፣ ይህ የተበላሸው ብድር ለደንበኛው ከተሰጠው ብድር ውስጥ ከ20 በመቶ እና ከዛ በላይ ከሆነ ሁሉም ብድሮች ወዲያው በተበላሸ ብድር መደብ ውስጥ እንዲካተቱ ታዟል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሌላ በኩል የባንኮች ብድር ውስን ቦታ ውሎ ፣እነዚያ ውስን ተበዳሪዎች የብድር መክፈል ውላቸውን በጊዜው መወጣት ባለመቻላቸው ባንኮች ላይ ሊመጣ የሚችል አደጋን ለመቀነስ ለአንድ ተበዳሪ ሊሰጥ የሚችል ብድር ላይ ጣርያ አበጅቷል። በተሻሻለው “የከፍተኛ ብድር ተጋላጭነት ገደብ መመሪያ” በሚለው ውስጥ ተካቷል። በዚህም መሰረት አንድ ባንክ ለአንድ ተበዳሪ የሚሰጠው ብድር ከባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ከ25 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት መመሪያው ያዛል።
መመሪያው ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር አንድ ተበዳሪ ቢወስድ እና ተበዳሪው መክፈል ባይችል ባንኩ ላይ ሊከሰት የሚችል ውድቀትን እና ባለ አክስዮኖችን እና ተያያዥ አካላት ላይ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ለመቀነስ ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል።
ብሄራዊ ባንክ በቅርቡ ያወጣው የፋይናንስ ዘርፍ መረጋጋት (stablity) ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ ባንኮች እስከ ዛሬ ከሰጡት ከሁለት ትሪሊየን ብር በላይ ብድር ከ20 በመቶ በላይ ማለትም ከ400 ቢሊየን ብር በላይ የሆነውን የወሰዱት ከ10 ተበዳሪዎች አይበልጡም ማለቱ፣ ብዙ ብድር ለጥቂት ተበዳሪዎች በመሰጠቱ ለፋይናንስ ዘርፉ ስጋት ፈጣሪ ነው አስብሏል። ስለዚህ ለአንድ ተበዳሪ ከአንድ ባንክ የሚሰጥ ብድር ገደብ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው ተብሏል።
ብሄራዊ ባንክ ካሻሻላቸው መመሪያዎች ውስጥ ከባንኮች ጋር ተዛማጅነት ላላቸው አካላት የሚሰጥ ብድር ላይም ገደብ ያስቀመጠ መመሪያም ይገኛል። ይህም የአንድ ባንክ ባለ አክስዮን ሆነው ከባንኩ የሚበደሩ ግለሰቦችንም ሆነ ኩባንያዎችን ሊያካትት ይችላል። በዚህ መልኩ የሚሰጥ ብድር ላይ ገደብ ማስቀመጥ ያስፈለገውም ብድር በአግባቡ እንዳይሰጥ እና የጥቅም ግጭትን ለማስቀረት ነው ተብሏል። በዚህም ከባንክ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተዛማጅነት ላላቸው አካላት በማንኛውም ጊዜ የሚሰጠው ብድር ከባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ከ15 በመቶ እንዳይበልጥም በተሻሻለው መመሪያ ገደብ ተቀምጧል።
ባንኮች ብድር ሲሰጡ ከነሱ ጋር ተዛማጅነት ላላቸው አካላት(ለባለ አክስዮኖችም ሆነ ሌላ) ሆነ ከባንኮቹ ጋር ተዛማጅ ላልሆኑ ግለሰቦችም ሆኑ ኩባንያዎች ተመሳሳይ መስፈርትን ይጠቀሙ ተብሏል። ይህም አንዳንድ ባንኮች ተዛማጅ ላልሆኑ ግለሰቦችም ሆነ ኩባንያዎች ብድር ለመስጠት የብድር መያዣንም ሆነ ሌሎች መስፈርቶችን ጠበቅ እያረጉ ለባለ አክስዮኖች እና ተዛማጅ አካላት ብድር የመስጫ መስፈርትን በማላላት የሚፈጽሙትን ኢ-ፍትሀዊነት ለማስቀረት በማሰብ ነው ።
27/12/2022
04/12/2022
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ለሚጠበቀው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሚያገለግሉ ስድስት የቦርድ አባላትን ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ሾሙ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል፡፡ የቦርዱ አባል በመሆን እንዲያገለግሉ የተሰየሙት ስድስቱ ተሿሚዎች ደግሞ፣ የሒሳብና የኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሒክመት አብደላ፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድምአገኝ ነገራ፣ በተመድ የካፒታል ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ኢዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የሴሬብሩስ ፍሮንቲየርስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ኃይለ ሚካኤልና የአዲስ አበባ ዩነቪርሲቲ ሌክቸረር አቶ አባተ አበበ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ኅዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)ን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡
እነዚህ የቦርድ አባላት ከኅዳር 21 ቀን 215 ዓ.ም. ጀምሮ የባለሥልጣኑ የቦርድ አባል ሆነው እንዲሠሩ መመደባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመቱን በሰጡበት ደብዳቤ ጠቅሰዋል፡፡
እነዚህ ተሿሚዎች በቦርድ አባልነት የተሰየሙት በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት ነው፡፡
በዚህ አዋጅ ውስጥ እነዚህ የቦርድ አባላት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት እንደሆነ ደንግጓል፡፡ ቦርድ አባላቱ ከኃላፊነት ስለመነሳት ወይም ስለመልቀቅ በሚለው አንቀጽ ሥር ማንኛውም የተሾመ የቦርድ አባል ኃላፊነት የሚነሳው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መልቀቂያ ጥያቄ ሲያቀርና የመልቀቂያው ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው የሚል ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡
የካፒታል ገበያ አዋጅ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የወጣ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ የዚህ አዋጅ መውጣት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ተደርገው ከተጠቀሱት ውስጥ፣ ካፒታል በመሰብሰብ የገንዘብ ሥርዓቱን በአዲስ ፈጠራዎች በመደገፍና የኢንቨስትመንት ሥጋቶችን የመጋራት አሠራርን በማስፋፋት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ የሚል ይገኝበታል፡፡
12/10/2022
ማስታወቂያ
ለግብር ከፋዮቻችን
የምእራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጥቅምት 1 የጀመረው የተጨማሪ ሰዓት ስራ እስከ ጥቅምት 30 ይቀጥላል!
የ2014 የግብር ዘመን ገቢ ማሳወቂያ ወቅት ከሐምሌ 1/2014 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል። ስለዚህ የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የገቢ ማሳወቂያ የመጨረሻው ወር አብዛኛው ግብር ከፋያችን የሚሳውቅበት መሆኑን ከግምት በማስባት ከጥቅምት 01 እስከ 30/2015 ዓ.ም ከሰኞ እስከ አርብ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ቅዳሜ ደግሞ ሙሉ ቀን አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
በገቢዎች ሚኒስቴር የምእራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
13/07/2022
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine)
እነማን መጠቀም አለባቸው?
ማናቸውም ሕግ ግዴታ የሚጥልባቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine) መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡
ከመሳሪያው ጠቀሜታዎች መካከል፡-
1. ሻጭ ድርጅቶች እስቶካቸውን ለማወቅና ለመቆጣጠር ይረዳቸዋል፣
2. በሽያጭ ሰራተኞችና የንግድ ድርጅቱ መካከል መተማመንን ያጠናክራል፣
3. በመሳሪያው የተመዘገበ ሽያጭ በህጋዊ ደረሰኝ የተደገፈ በመሆኑ ገዢው በንግድ ድርጅቱ ላይ የበለጠ አመኔታን ያሳድራል፣
4. መሳሪያው የሚመዘግበው የግብይት መረጃ ለታክስ አስተዳደሩ ፍትሐዊ የግብር ውሳኔ እንዲያከናውን ያግዘዋል፣
5. በተዘዋዋሪም ጤናማ የገበያ ውድድር እንዲኖር ከመርዳቱም በተጨማሪ መሳርያው በግብይት ወቅት ደረሰኝ ስለሚያዘጋጅ ገዢዎች የሚከፍሉት ታክስ በትክክል ለመንግስት ገቢ ለመደረጉ እርግጠኝነት ይሰማቸዋል፡፡
የመሳሪያው ተጠቃሚዎች ማድረግ ከሌለባቸው ነገሮች መካካል፡-
1. እውቅና ያልተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም፤
2. በሚኒስቴሩ ዘንድ ያልተመዘገበ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም፤
3. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያውን ከተርሚናል ጋር አለማያያዝ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine) ተጠቃሚዎች ማድረግ ከሌለባችሁ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን አርብ ማታ ከ3፡00 ጀምሮ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ
በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን
እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!