07/05/2024
አላህ ወአክበር
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawlet Ahmed - ሐውለት አህመድ, Financial Consultant, Addis Ababa.
07/05/2024
አላህ ወአክበር
10/01/2024
የአድዋ ሙዚየምን የሰሩ እጆች የተባረኩ ናቸው።
10/01/2024
ደብረ ብርሃን ... ከዚያም ... ጣርማ በር ዋሻን አልፌ መሔድ ናፈቀኝ። ሰው ሲከፋው ወዴት ነው የሚሄደው? እኔ ብዙ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢዬ ነበር ቱርርርር ብዬ የምሔደው። ወይ ጉድ! ሲከፋ ብን ብሎ መጥፊያም በሩ ሊዘጋ ይችላል ለካ! 😥
ደብረ ብርሃን ❤️ እንዳ'ንቺ የምወደው ከተማ በምድር ላይ የለም። 😥
ትናንት አንድ የሕይወት ምዕራፍ ዘጋሁ። የ ፒኤች ዲ መመረቂያ ሥራዬን በአሪፍ defend አድርጌ የ4 ዓመት አስደሳች፣ አድካሚ እንዲሁም አልፎ አልፎ አሰልቺ የነበረውን ዘለግ ያለ ጊዜ አጠናቀቅሁ። አልሃምዱሊላህ! ደስ ይላል።
እና የ Viva Voce ኮሚቴው መመረቂያ ሥራዬ ለ ''Best Thesis/Dissertation Award'' እንዲወዳደር መርጦታል። ይሄም ደስ ይላል። ❤️
አንደኛው external examiner ፔፐሬን ''what a master piece!'' ብሎ ካደናነቀው በኋላ ከ30 በላይ ጥያቄ ያዘነበብኝም አስደሳች ነገር ነበር። 😊❤️
በዚህ ጉዞ ላይ አብራችሁኝ የነበራችሁትን ሁሉ እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ። ሌላ ጊዜ በሥም ጠርቼ አመሰግናችኋለሁ።
🙏🙏🙏
01/01/2024
ሰበር ዜና!
ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች
****************
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች።
30/12/2023
የነጋድራስ TV show ዳኞች
የምዕራፍ 1 ውድድር በስኬት ተጠናቋል።
ለምዕራፍ 2 ውድድር ተዘጋጁ።
30/12/2023
ተስፋዬ ገብረአብ አወዛጋቢ ደራሲ ነው። ቅዱስ ብለው የሚጠሩትን ያህል እርኩስ የሚሉት ስሙ እንዲጠራ የማይፈልጉ ሚሊዮኖች አሉ። እኔ በበኩሌ የተስፋዬ ብዕር አድናቂ ነኝ። በአወዛጋቢ ስብእናው ዙሪያ የሚቀርቡ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ክርክሮች ሁለተኛ ጉዳዮች ናቸው።
«የአድአው ጥቁር አፈር» በሚል ወጣቱ ደራሲ ጉቺ ሽመልስ ለህትመት ያበቃውን መጽሐፍ አንብቤው ደራሲው ልክ እንደተስፋዬ ገብረአብ ብዕር የሚታዘዝለት መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ። አቅሙ ያላችሁ ሁሉ መጽሀፉን ገዝታችው እንድታነቡ ጊዜ ያላችሁ ደግሞ ዛሬ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በስካይላይት ሆቴል/አዲስአበባ በመገኘት የምጽሀፍ ምረቃውን እንድትታደሙ እጋብዛለሁ።
ለመቃወም ማንበብና ወቅ አስፈላጊ ነው።
29/12/2023
የሕትመት ዋጋ በከፍተኛ መጠን መናር የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ''አሽር ቤት'' መጽሐፍ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ሕትመት ስትገባ በአንድ መጽሐፍ እስከ 50 ብር ጭማሪ ተጠይቋል። በጣም ጥቂት ኮፒዎች መቅረታቸውን ተከትሎ ለሶስተኛ ጊዜ ለማሳተም ዋጋ ጠይቄ በፊት ከታተመበት የመቶ ሃምሳ ምናምን ብር ጭማሪ አለው።
እናም ፊታችንን ወደ ዲጂታል አማራጭ ማዞር አይነተኛ መፍትሔ ሆኖ አግኝተነዋል።
''አሽር ቤት'' Tuba Books (ቱባ መጻሕፍት) app ላይ ተጭናለች። የመሸጫ ዋጋዋም በጣም ቅናሽ ስለሆነ ወረድ ወረድ አድርጋችሁ ተዝናኑባት። (ሊንክ 👉 ኮመንት መስጫ ሳጥን) 😊
በሃርድ ኮፒ የምትፈልጓት ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር (ለገሐር ኮሜርስ አጠገብ)፣ Abdu Book Delivery (ጊዮርጊስ) እና አል-ተውባ መጻሕፍት መደብር (አንዋር መስጊድ) ታገኟታላችሁ። 🙏
አሸር ቤት መጽሀፌን ቱባ Tuba books (ቱባ መጻሕፍት) app ላይ ታጋኟታላችሁ። ማንበብ ሙሉ ያደርጋል። በቅናሽ ዋጋ አውርዳችሁ በማንበብ እራሳችሁን ሙሉ አድርጉ።
እሁድ ሰልፍ አይቀርም !!!!!!!!!!
27/11/2023
መሪዬ ይናፍቀኛል 🤔
ይመጣሉ 💪